የዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አመራር አካል ከትናንት ወዲያው ትናንት፣ ከትናንቱ ዛሬ በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙት የማን አለብኝነት በደል እየዋለ እያደረ በየእለቱ እያየለ እየከፋ እየከረፋ መጣ፡፡ ከቀድሞው የቦርድ ሊቀመንበር ጋር የውረዱ አልወርድም እንካሰላንቲያ ከተጀመረ ግዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ቤተክርስቲያኗ እንደተናጠች አመት ያህል አስቆጠረች፡፡ ባለፈው ጽሑፌ እንዳመላከትኳችሁ አዲሱ ቦርድ የቀድሞው ሊቀመንበር ጥቅም አስከባሪዎችና የአዲስ ፖለቲከኞች መጢቃ ነው፡፡ የቀድሞው ሊቀመንበር ዋና ጥቅም አስከባሪ አድርገው ያሰቧችውን ደብተራ በባለግልሲኖዶሱ በሻለቃ መልከፄዴቅ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ አድርገው ሲያስሾሙ የተቀጣጠለው የተቃውሞ እሳት ላይ ቤንዚን እንደመቸለስ ሆነና እሳቱ ከቁጥጥር ውጭ ተዛመተ፡፡
ከኢራቁ ሳዳም ሁሴን፣ ከሊቢያው ጋዳፊ፣ ከግብፁ ሙባረክ የታሪክ መጽሐፍ ላይ አንዱን ገጽ ገንጥለው በመውሰድ ለራሳቸውም ያልበጀውን የማንጠይቆኝ አገዛዝ ይሁነን ብለው ተያያዙት፡፡ ለጥፋት ተግተዋልና ከዚያ በኋላ የተጻፈውን የአወዳደቃቸውን ገጽ ለማንበብ ግን ዝንባሌም ግዜም አልነበራቸውም፡፡ ባለፉት አሥራአምስት ዓመታት ውስጥ በምንም መልኩ ሃሳቡን ተጠይቆ፣ አስተያየቱን ሰጥቶ፣ ስሜቱን እንዲተነፍስ ያልተፈቀደለት ምዕመን አምላኩን ፈርቶ የተላበሰውን ዝምታ እብሪተኞች እንደፍርሃት ቆጠሩበት፡፡ መቼም ልብ ሲያብጥ ድፍረት ይሰማልና በስተመጨረሻ የወንጌል መምህሩንና ለአሥራ አራት አመታት ያለምንም ክፍያ ያገለገሉ አራት ዲያቆናትን ከመቅደስ ለማሰናበት በቁ፡፡ ቤተከርሲቲያኑ የራሱን ሕንፃ ከመግዛቱ ቀደም ብሎ፣ እነዚህ ወጣት ዲያቆናት በብፁዕ አቡነ ሣሙኤል እየተስተማሩና እየታዘዙ እሁድ በጥዋት መቅደሱን እያዘጋጁ ድንኳኑን እየተከሉ፣ ከአገልግሎት በኋላ እየነቀሉ ተሸክመው ከቦታ ቦታ እያዘዋወሩ ካነጹት ቤተክርስቲያን፣ በዕምነት አልባ ፖለቲከኞች፣ በጠባብ ብሔረተኞችና ጎጠኞች፣ በእበላባይ ሆዳሞችና ጊዜያዊ ጉልበተኞች አምላካቸውን ከሚያገለግሉብት፣ ከሚያወድሱበት መቅደስ ተገለሉ፡፡
ይህ እርምጃ የሚገመገመው በተከታታይ ከተወሰዱ ተመሳሳይ እርምጃዎች ጋር በጋራ እንጂ ብቻውን በተናጠል ምንም ቤት አይመታም፡፡ በአብያተክርስቲያናትና በኦርቶዶክሳውያን ሕዝበ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቷል፡፡ የሕዝቡን እይታ ያልያዘበት ምክንያት ምናልባትም እንደ ግራኝ መሐመድ ወረራ ከእምነቱ ውጭ የመጣ ስላልሆነና የሰው ህይወት ስላልተዋደቀበት ሊሆን ይችላል የሚል የራሴ ግምት አለኝ፡፡ ስፋቱና ጥልቀቱ ከዚያን ግዜው ከማነሱ በስተቀር በመጨረሻ ሊያደርስ የሚችለው ጥፋት ግን እያዘገመ የሚጓዝ እምነታችን ላይ እንደዘንዶ በመጠምጠም ላይ ያለ ነቀርሳ መሆኑን መጠራጠር እንደሰጎን እራስን አሸዋ ውስጥ ምቅበር ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው ሳይውል ሳያደር በተለያዩ እስቴቶች ያሉ ለዚህ ጦርነት ሰለባ የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ሕዝበ ከርስቲያን በሙሉ ሊዋጉት ይገባል የሚል ጠንካራ እምነት ያለኝ፡፡
እሰካሁን አልጠረጠራችሁ እንደሆን፣ ይህንን የሃይማኖት ጦርነት በፊታውራሪነት የሚመሩት ብፁዕ ሻለቃ መልከፄዴቅ ናቸው፡፡ ጦርነቱ የተከፈተው በመጀመሪያ ከማስተማርና እራሳቸውን ለተሻለ የወንጌል አገልግሎት የበለጠ ለማጎልበት ከትምህርት ቤት ትምህርት ቤት ሲሯሯጡ ለራሳቸው ክብርንና ልዩ ስፍራን ጠይቀው የማያውቁትን ወንጌላዊው አባ ገብረሥላሴ ጥበቡን ወንጌልን ከሚሰብኩበት አውደምሕረት በማስባረር ነበር፡፡ መቼም እውነትን መናገር፣ ለእውነት መቆም ወንጀል በሆነበት ቦታ ደፍሮ እውነትን መናገር ለእውነት መቆም ከመባረርና ክመሳደድ አልፎ የሕይወትም ዋጋ ጭምር ሊጠይቅ ይችላል፡፡ አባ ገብረሥላሴ የተሳደዱት ለእውነት መቆማቸው እንደጥፋት ተቆጥሮባቸው ነው፡፡ ዋናዋ ሰለባ የሆነችውና በመስቀል ላይ የተቸነከረችው ግን እውነት እራሷ ሆነች! አባ ገብረሥላሴ ግን ባላመኑ አረማውያን እጅ የወንጌላውያንን ፀጋ በክብር ተቀበሉ፡፡
በሻለቃ መልከፄዴቅ የሚመራው ማለትም በደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከቀድሞው ቦርድ ሊቀመንበር፣ ጎጠኛ ደጋፊዎቻቸው፣ የሲኖዶስ ድጋፍ ሰጪ ኮማንዶ ብርጌድ በአንድ ወገን እና በኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት ኦርቶዶከስውያን በሌላ ወገን ሆነው የተፈጠረውን አለመግባባት ለማርገብ በሠላሳ ሁለተኛው የሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ በተደረገው ውሳኔ መሠረት ሶስት አባላትን፤ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብን ከአትላንታ፣ ብፁእ አቡነ ዮሴፍን ከላስቬጋስ እና አባ ገበረሥላሴ ጥበቡን ከሲያትል፤ ያቀፈ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ቦታው መጥቶ ነበር፡፡ በዚህም ተልእኮው ቡድኑ መዕመናኑን በቡድንና በተናጠል፣ የአመራር አካላትን በቡድን፣ ሊቀመንበሩን በግል በማወያየት የራሱ ውሳኔ ላይ በመድረስ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ምርጫ ለማካሄድ ውሳኔ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ ፍትህ የሚባል ቃል ለጆሯቸው እንግዳ የሆነባቸው ሊቀመንበር ምርጫው በፍትህ ከተካሄደ የፈለጉትን ማስመረጥ ስለማይችሉ ያላቸው ዕድል ሂደቱን ማሰናከል ብቻ መሆኑን ስለተረዱት ጎሮዶማኖቻቸውን ቀስቅሰው በቡድኑ አባላት ሕይወት ላይ ዛቻ ተላለፈባቸው፡፡ ሊቀመንበሩም ልትገደሉ ነውና ባስቸኳይ ወደ መጣችሁበት ጥፉ የሚሉ ሁለት ደብዳቤዎች ጻፉላቸው፡፡ ዛቻውንም እውነታ ለመስጠት ክጎሮዶማኖቹ አንዱ አንደኛው ሊቀጳጳስ መኝታ ቤት ገብቶ ሲዝትባቸው አሁንም ሆነ ወደፊት ቤቱ ከክርስትና ውጭ የሆነና ምንም ተስፋ የሌለው መሆኑን በመረዳት ይመስላል በማግስቱ ሁለም ሁሉንም ጥለውት ወደየመጡበት የተመለሱት፡፡ ፎካሪው እንግዲህ እስካሁን ከየትም ይሁን ከየት ካሳ አግኝቶ እንደ ሆነ ግን የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ባሳዩት ጠንካራ አቅዋም ነው እንግዲህ መነኩሴው አባ ገብረሥላሴ መስዋዕትነትን የከፈሉት፡፡
ሁለተኛው የሻለቃው ሰለባ ሊሆኑ ተዶልቶባቸው የነበሩት የሳንዲዬጎው መነኩሴ መምህር አባት ካህን አባ ቃለጽድቅ ነበሩ፡፡ ከቦርድ አባሎቻቸው ጋር ዶልተው በሳምንቱ እሑድ በሕዝብ ፊት አዋርደው ሊያባርሯቸው ያሰቧቸው መነኩሴ አንድ ሳምንት ቀደም ብለው ደህና ይሰንብቱ ብለው ከመቶ ዘጠናው ጤነኛ ምዕመን ተከትሏቸው ነጎዱ፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ እኒህ እብሪተኛ የአዋቂ አጥፊ አረጋዊ ሻለቃ የገነቡት በድቡሽት ላይ እነደሆነ የተከሰተላቸው፡፡ አንበሳ አጋጠማቸውና ተደቆሱ፡፡ እንግዲህ በተረፏቸው አስር ምዕመን $2 ሚሊዮን የሞርጌጅ ዕዳ ሲከፍሉ ለማየት በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ ወይስ እዚህ ዲሲ የተዘጋጀችላቸው አንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ እየኖሩ በቋሚነት ውጊያውን ከዚህ ሊመሩት ይሆን? ወይም ቦልቲሞር ባለው አምባቸው ውስጥ መሽገው መታኮሱንም ይሞክሩት ይሆናል፡፡ አምባው እንኳን የሚረባም አይደል፣ ብቻ ይሞክሩት፡፡
ኦክላንድ ተቀደምኩ በሚል ቁጭት ዋሽንግተን ያለውን ሰባኬ ወንጌል እንደኔ እንዳትሆኑ ሳይቀድማችሁ ቅደሙት የሚል ምክር ለግሰው አስባረሩት፡፡ ለነገሩ በአንድ አሁን የአመኔታ ጉባኤ አባል በሆነ ዘማሪ ግፊት ማንም ምዕመን ባልተቀበለው የሻለቃ መልከፄዴቅ ተሿሚ አስተዳዳሪ ደብተራ አስተባባሪነት በቀድሞው ሊቀመንበር ወሳኝነት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የወንጌል ትምህርት ከታገደ ወደ ስድስት ወር ያህል ይጠጋዋል፡፡ መቼም አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ የሰው ገንዘብ አትመኝ ወዘተ. የሚሉት ትዕዛዛት ካልተሻሩ በስተቀር የጌታ ወንጌል በኛ ቤተክርስቲያን እምብዛም ወዳጅ የምታፈራ አትመስልም፡፡ ከተጻፈች ወደ ሁለት ሺ ዓመት የሆናትን ወንጌል ለአንዳንዶች ተብሎ አሁን መቀየር ደሞ በቀላሉ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሰባኬ ወንጌሉ ሲያስተምር በቀጥታ እነሱን የተናገረ እየመሰላቸው ዐይናቸው ደም ይለብሳል፡፡ መቼም ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም አይደል ነገሩ፡፡ የወንድማቸው የመምህሩ መታገድ ያሳዘናቸው ዲያቆናት ጉዳዩ ክርስቲያናዊ እንዳልሆነ ተቃውሟቸውን ለማስመዝገብ ለታኅሳስ ገብርኤል ንግሥ ዕለት ሳይገኙ ቀሩ፡፡ ይህን ቀን አስበውበት የመረጡት ሳይሆን ቦርዱ ውሳኔውን ያስታወቀው በዓሉ ጥቂት ቀን ሲቀረው በመሆኑ ቀኑን የመረጠው እራሱ ቦርዱ ነው ማለት ይቻላል፡፡ መምህሩ ድርብ በደል እንደተፈፀመበትም ይነገራል፡፡ ክህነትን የመስጠት ሥልጣን የሊቀ ጳጳሱ ሆኖ ሳለ ከበታቻቸው ላለ ደብተራ አላስታወቁም በሚል ሰንካላ ምክንያት ሊሰጠው የነበረው የክህነት ሹመቱ እንዲታገድበት ሲደረግ እግረመንገዳቸውንም አንድ ሊቀጳጳስ በቤትክርስቲያን ውስጥ ሊኖረው የሚገባን በእግዚአብሔር የተቀባ ሥልጣን ፀረ ክርስቶሳውያን ሽረውታል፡፡ ያደቆነ ሠይጣን ሳያቀስስ አይለቅም ነውና ነገሩ ዲያቆናቱንም አብረው አሳደዷቸው፡፡ ይህ ትዕዛዝ የተላለፈው በቀጥታ ከጦር አዛዣቸው ከሻለቃ መልከፄዴቅ እንደሆነ ከራሳቸው ከአንደበታቸው የሰሙ ያረጋግጣሉ፡፡ ቅስናውን በተመለከተ ግን በአንድ በእንግድነት ለረዥም ዓምታት ቤተክርስቲያን ውስጥ በኖሩ ጳጳስ ሁለት ግዜ ላገቡ ግለሰብ ቅስና ሲሰጡ ማንም ለማንም የነገረም ያስነገረም አልነበረም፡፡
በዚህ ባለፈው እሑድ የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ ዕለት ለመብታቸው በቁርጠኝንት በመቆም ምዕመናን ትልቅ ጀብዱ ያካናወኑበት ታላቅ ቀን ሆኖ ውሏል፡፡ የአሜሪካን አገር ህገመንግሥት ቁልጭ አድርጎ የፈቀደውን የመጻፍ፣ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመናገር፣ የመቃወም መብት ሳይጠቅምበት በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለአመታት እንደከብት እየተነዳ የኖረው ሕዝብ በዚያን ዕለት ቁጣው ገንፍሎበት ታምቆ የኖረ ስሜቱን ያንፀባረቀበት የተቀደሰ ዕለት ነበር፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ አሳሳቢ ሁኔታ ያሳሰባቸው ምዕምናን በፓትርያርኩ ፊት ቀርበው በሚገባ ችግራቸውን አሳውቀዋል፡፡ ታዲያ ተሳታፊዎቹ በብዛት እህቶቻችንና እናቶቻችን ሲሆኑ ጥቂት ጠንካራ ወንድሞቻችንም ታክለውበት ነበር፡፡ የወንዶቹ ቁጥር ሳሳ ማለቱ ግን አንድም ጉዳዩ አልገባቸውም ወይም ለእምነታቸው ብዙም ተጨናቂ አይደሉም ያሰኛል፡፡ ወንዱ ምን ነካው? መብቱን አያውቅም ወይስ ከቀይ ሽብሩ ሰቆቃ ገና አልባነነም? አንዳንድ የቀይ ሽብር አራማጆች የነበሩትን በቅርብ የሚያውቃችውን ግለሰቦች በአካባቢው ሲያያቸው አሁንም ያባንነው ይሆን? እግዚአብሔር ዕምነታቸውን ያጽናላቸው፣ ተልእኳቸውን ይግለጽላቸው!
ይህን አበሻ በይሉኝታ አፉን የያዘበት አኗኗር የጣማቸው ተመራጮች በቤተክርስቲያኒቱ አዲስ መተዳደሪያ ደንብ አሁንም የመዕመኑን አፍ ለማሸግ ሞክረዋል፡፡ ምንኛ ዝቅ ያለ አስተሳሰብ የተንሰራፋባቸው ሰዎች በመካከላችን እንዳሉ ሳስበው በውነት ይዘገንነኛል፡፡ የአንድ ቤተክርስቲያን የመተዳደሪያ ደንብ ከአሜሪካ ህገመንግስት በላይ ቀደምትነት ይኖረዋል ብሎ ማውራትና ማስወራት ትርፉ ትዝብት ላይ መውደቅ ነው፡፡
ልብ በሉ እንግዲህ ቤተክርስቲያን በውስጧ ምን ዓይነት ሰዎችን እንደያዘች፡፡ እኛጋ እንደምናየው የሚመሯት ከጦር አዝማች ሻለቃቸው ጀምሮ በተዋረድ እምነት የሌላቸው ፖለቲከኞች፣ የአገር ፍቅር የሌላቸው ጎጠኞች፣ ፍቅረ ነዋይ የተጠናወታቸው ስግብግቦች መሆናቸውን የተገነዘብን ይመስለኛል፡፡ እውነትንም እንደክርስቶስ በመስቀል ላይ የቸነከሯት እነዚሁ ሃይማኖተ ቢስ ከሀዲዎች ናቸው፡፡ ጥቂት ጎጠኞች ለአንድ ሙሉ ክፍለሀገር ስም መነሻ መሆናቸው ያሳዝነኛል፡፡
ወንድማችሁ ኃይለገብርኤል ታደገ
የዋሽንግትኑ ቅዱስ ገብራኤል ቤተክርስቲያን መእመናን እነሆ የሰይጣን በሆነ መንፈስ መታወክ ከተያያዛቸው በግልጽ አስርስምንት ወራት ገደማ ሆናቸዉ። ለዚህ ኣኩይ ትግባር ድግሞ አንደተደጋገመዉ ከቀድሞዉ ቦርድ ጀምሮ በተሸረበ የሰንሰለት ገመድ የትብተባዉ ተባባ