የግሌ ሲኖዶስ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከማንኛውም የኢትዮጵያ የክርስቲያን ዕምንት ተቋማት በሙሉ በተለየ ሆኔታ በሁለት ሲኖዶሶች የሚወከል የዕምነት ማዕከል ሲሆን የአንዱ ውክልና በሀገር ውስጥ የሌላው ደግሞ በባሕር ማዶ መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡ ታዲያ የባህር ማዶው ሲኖዶስ የተቋቋመው የአገር ውስጡን ተቃውሞ ስለነበር ሁለቱ ሲኖዶሶች ዓይን ለዓይን የማይተያዩ ጠላቶች ናቸው፡
በስደተኛው ሲኖዶስ አባባል ፓትርያርክ በሕይወት እያለ በላዩ ላይ ሌላ አይሾምበትም የሚለው መሠረታዊ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ የዘረኝነትም ጉዳይ ትልቅ ሥፍራን የያዘ ነጥብ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም አዲስ ተሿሚ ምንጊዜም ቢሆን የራሱን የቅርብ ታማኞች ይዞ ስለሚመጣ የቀድሞዎቹ የቤተክህነት መሪዎች ውሎ አድሮ ቦታቸውን መነጠቃቸውም አይቀሬ መሆኑንም ከወዲሁ የተረዱት ይመስላል፡፡ በተለይም የስደተኛው ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የዕድሜ ባለፀጋ ሊቀጳጳስ ቀደም ሲልም ለአጼ ኃይለሥላሴ መንግሥት በአማካሪነትም ያገለገሉ ስለነበሩ የሥልጣን መንጠላጠያ መሰላሏንና መሽሎክሎኪያ ቀዳዳዋን፤ ሥልጣን ስትመጣ መጣፈጧን ስትታጣ ምሬቷን ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለነበሩ ከሃይማኖት አባትነቱ ይልቅ የፖለቲካውን የረቀቀ ፍትጊያ ይበልጥ ያጣጥሙ እንደነበር ይነገርላቸዋል፡፡ ፖለቲከኝነት በራሱ ነውር ባይሆንም ከሃይማኖት አባትነት ጋር ግን በፍጹም እጅ ለእጅ ተያይዞ አይሄድም፡፡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ደግሞ ለራሱ ለእግዚአበሄር ሊሆን ይገባዋል፡፡ ለሁለት ጌታ ሊገብሩ የሞከሩ ግዜ ነው ከሁለቱም ሳይሆኑ የቀሩት፡፡
አንድ የሚሠራውን የሚያውቅ ተቃዋሚ ድርጅት ሌላው ቢቀር በምንም ዓይነት ቢሆን ተቃውሞት የተነሳውን ድርጅት የጥፋት ጎዳና መከተል በራሱ የዝቅጠቱ መነሻ ምልክት ነው፡፡ የሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊ ከምንምና ክማንም በላይ ዓይናቸው ሥልጣናቸውን ማጠናከሩ ላይ ስለነበር በአራት ነባር ሊቀጳጳሳት ጥንስስነት ዘጠኝ ጳጳሳትን በመሾም ሲኖዶሱን ከመሠረቱና ካስመሠረቱ በኋላ ከዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ገብርኤልና ክቦልቲሞር ቤተክርሰቲያናት ታማኝ ወገኖቻቸውን መልምለው ክቃለ አዋዲው ውጭ “የሲኖዶስ ድጋፍ ሰጪ” በሚል መጠሪያ አንድ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ ተወርዋሪ ጦር ፈጥረዋል፡፡ ይህም ለበርካታ ወጣቶች ሕይወት ህልፈት ተጠያቂ የሆነው የቀድሞ የቀይ ሽብር ኮሚቴ አባላትን፣ግልብጥ ካቶሊኮችንና ቤተክርስቲያን ውስጥ አንዲት ቀን እንኳን ገብተው አስቀድሰው የማያውቁ ከእግዚአብሔር ካሳ የማይገባቸው ዕምነት አልባ ፖለቲከኞን ያካተተ ሽብር ፈጣሪ የሚሲዮን ጦር በመሠረቱ የተመለመለው ከደብረታቦር አውራጃ ባብላጫም ፋርጣ በመባል ከምትታወቅ አንዲት ወረዳና አንዳንድ ጀምበር ከጠለቀባቸው ወዶ ገባዎች መሃል መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ክሆነ ሰንብቷል፡፡ መቼም እንደሳቸው ካለ አረጋዊ የኃይማኖት አባት ምዕመንን በዘር መለየት የማይጠበቅ ቢሆንም ምንም ቢሆን ካገር ልጅ በላይ የሚታመን የለም፣ ሌላው ምን ያረጋል፣ በሚል እሳቤ የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ከጥንት ባሕሪያቸውን የሚያውቁ በሕይወት ያሉ ምስክሮች ሞልተዋል፡፡
በዚህ ዓይነት ጠባብ ብሔረተኝነት የተወጣጠረ የበላይ አካል በስሩ ምን ዓይነት አብያተክርስቲያናት እንዳቀፈ ወይም እንዳካተተ ለማየት እንዲረዳ ከሩቅም ከቅርብም ከውጭም ከውስጥም ንጹሕ ህሊና ባላቸው ኢትዮጵያውያን አነሳሽነት አንድ በውል ያጠናሁትን ቤተክርስቲያን ጉዳይ በተምሳሌነት ላውጋችሁ፡፡
በኖርዝ ኢስት ዋሽንግትን ዲሲ ክፍለከተማ ብላደንስበርግ መንገድ ላይ የሚገኘውን ደብረኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን የምታውቁት መቼም ታውቁታላችሁ፡፡ ቤተክርስቲያኑን ላለፉት አሥራ አምስት ዓመታት በቦርድ ሊቀመንበርነት የመሩት ግለሰብ የመጡት ከፍ ብለው ከተጠቀሱት የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ጋር ካንድ ወረዳ በመሆኑ ከነፍስ አባታቸው ብዙ ትምህርት ሳያገኙ አልቀሩም ብዬ አስባለሁ፡፡ በመሠረቱ ጎሮዶማኖቻቸው በሃርቫርድ ምሩቅነታቸው የሚያወድሷቸው እኒህ ሊቀመንበር ለሥልጣን ባላቸው ልዩ ጥም ከነፍስ አባታቸው የሚተናነሱ ባይሆኑም የእነዚህ ሁለቱ ሰዎች ለሥልጣን ሟችነታቸው ግብ ግን እየቅል ነው፡፡
እኒህ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለመንግሥትና ለስለላ ድርጅቱም ጭምር በሰጡት አገልግሎት ታዋቂነትን ያተረፉት ሊቀጳጳስ ከምንም በላይ ትልቅ ነኝ ብሎ መኮፈስንና ከንቱ ውዳሴን ከልክ ባላይ ስለሚወዱ ይህን ነባር ሱሳቸውን የሚያረካላቸው ማንም ብልጣብልጥ አምታታው በከተማ እንደ ህጻን ልጅ እጃቸውን እየጎተተ ሊጫወትባቸው እንደሚችል በተዳጋጋሚ ታይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ በፊት የቅዱስ ገበርኤል ቤተክርስቲያን ሊቀመንበርነታቸውን ከአሥራ አምስት ዓምታት በኋላ በብርቱ ግብግብ ያስረክቡት ግለሰብ ይህን ሱስ በትክክል ስለተረዱላቸው ከንቱ ውዳሴውን ጎንበስ ቀና፣ እጥፍ ዘርጋ በማለት ያለምንም ገደብ ያረኩላቸዋል፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በተንኮል፣ ምዕመንን ክምዕመን፣ ካህንን ክካህን በማጋጨት የሚታወቁትና በሲኦል ደቼ ያቦኩት የመርዝ እርሿቸውን በመቅደስ ውስጥ በጥብጠው የረጩትን ተስፋ የሌላችው ተስፈኛ በአስተዳዳሪነት ለማስሾም የተጠቀሙበት ዘዴ ያንኑ መከረኛ የፋርጣ ተወላጅነታቸውንና ሿሚው የሚወዱትን ከንቱ ውዳሴ በማቅረብ ነበር፡፡
ሊቀመንበሩን እንኳን መቼም አምላክ መሐሪ ነውና ይምራቸው እንደሁ እንጂ ሥራቸው እንኳን ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያደርሳቸው አይመስልም፡፡ ሁሉንም ይወዱታል፣ በተለይም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ካለው፡፡ የሕይወታቸውን መስመር ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል በሚል ፍልስፍና ላይ የመሠረቱ ስለሆነ በዚህ በመሸበት ዕድሜያቸው ይለወጣሉ ብሎ ማሰብ ከንቱ ሕልም ይሆናል፡፡ አንዲት ትንሽ ቤተክርስቲያን በቅጡ መምራት ተስኗቸው የሚደነባበሩ ሰው በጎሮዶማኖቻቸው አፍ ጋሼ ጋሼ ተብሎ መጠራትን ፣ አገር ይመራሉ ተብሎ መሞካሸቱንና ከንቱ ውዳሴን እንደ እውነት ይቀበሉታል፡፡ ጭንቅላታቸውን ደመና ውሰጥ ክተው በፍጥነት በመንደርደር ላይ ያለውን የውርደታቸውን ድግሰና የታምቡር ድለቃ ክማየት የጋረዳቸውም ይሄው ከንቱ ውዳሴን አምነው መቀበላቸው ነው፡፡
አሁን በግልጽ እየታየ እንደመጣው ሁን ተብሎ የተያዘው አማራጭ ግን ክሕግ በላይ በመሆን ለማንም ተጠያቂነት የለብኝም ወደሚል ወለል የለሽ አዘቅጥ እየወረዱ ይመስላል፡፡ ቀደም ብሎ ከላይ እንደተመለከትነው እሳቸውም የግል ጠባቂ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ ጦር ከዚያችው ከጎጣቸው ቀደም ብለው ማደራጀታቸው የቁርጡ ለት ቀኑን ጠብቆ ተከሰተ፡፡ ይህ ስመጥፉ ይሉኝታቢስ የቅጥረኞች ጦር በእውነተኛ የእግዚአብሔር መንገድ የሚጓዙ ምዕመናንን ጥሩ ስም የማጉደፍ ፀያፍ ተግባር ላይ በመሰማራት ሰንካላ አስተዳደጋቸውን ፍንትው አድርገው ፀሐይ ላይ አስጥተውታል፡፡ ሕዝብ ሊቀመንበሩ እንዲወርዱ ሲጠይቅ እንዲቆዩ በመምከርና ሌሎች መሰሎቻቸውን በጎጥ በማደራጀት ጥያቄውን ለመቀልበስ መታገል፣ ሂሳባቸው ይመርመር የሚል ጥያቄ ሲነሳማ ጭራሽ እንደ አዶከብሬ የሚያስጓራቸው ለጉድ ያስቀመጣቸው ጉዶች ናቸው፡፡
ከጎጠኞቹ ሌላ ለዚህ ተግባር የተሰለፉት ምልምል የወሬ ኮማንዶዎች ተአማኒነታቸው የተገዛው አነሰም በዛ በገንዘብና በልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ነው፡፡ ከንዋየ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ያለ ምንም ቁጥጥርና የዋጋ ተመን ዕቃ አስገብታ ምን ያህል እንዳቀረበች እንኳን ሳይታወቅ ቸርችራ ከምትጨርሰው ወይዘሪት ጀምሮ፣ ከነልጆቿ ወደ ኢትዮጵያ ደርሶ መልስ ያይሮፕላን ቲኬት የሚገዛላትን እመቤት፣ ልዩ ብድር የተሰጠውን ወጣት የልጆች አባት፣ ለቤተክርስቲያኑ ገቢ ለማስገኘት ታስቦ እንዲሸጥ በአደራ የተስጠውን ዲቪዲ ሽጦ በኪሱ የከተተውን የመሳሰሉት የሥርአቱ ግንባር ቀደም አጥፍቶ ጠፊ ወንበዴዎች ቋሚ ምሳሌዎቸ ናችው፡፡ በርዳታ የሚመጣ ዕቃ ተሽጥ ከሚገኘው ገቢ የሚቃመሱትም ቢሆኑ የበሉት ሆዳቸውን እየቆረጣቸው ምርመራን ለማጨናገፍ በሚደረገው ንቅናቄ በመሳተፍ ለበሉበት እየጮሁ ናቸው::
መቼም ገደብ የሌለው ሥልጣን የሚሠሩትን ያሳጣ የል፤ ሊቀመንበሩ በአንድ ወቅት ሊቀጳጳስ አንስቼ በሌላ ሊቀጳጳስ እተካለሁ ብለው ተነስተው ነበር፡፡የት የተቀበሉት ክህነት ለዚህ ክብር እንዳበቃቸው ባላውቅም፣ ምናልባት እሱም በሚስጥር በመንደር ልጅነት መታደል ጀምሮ እንደሆን የሚል ስጋት አለኝ፡፡ ለማንኛውም ላለፉት አሥራ ስምንት ዐመታት ረሃብን ሳይቀር በብዙ ችግርና በብዙ መክራ ውስጥ ያለፉትን ሊቀጳጳስ፣ ቁምስቅላቸውን ሲያሳዩአቸው የኖሩት አልበቃ ብሏቸው እሳቸውን አባረው በቦታቸው ሌላ ለመተካት የማይታክት የማይጠግብ ዐይናችውን ወደ እንግሊዝ አገር አሻገሩት፡፡ከሃያ ዐመታት በላይ እንግሊዝ አገር ሲኖሩ ቢያንስ አስር ሰው እንኳን አሰባስበው ለስማቸው መጠሪያ አንዲት ትንሽ ቤተክርስቲያን መመሥረት ያቃታቸው፣ ከሰው ተስማምተው መኖር ያልቻሉ ሊቀጳጳስ ከባሕር ማዶ ለማስመጣት በቁ፡፡ በማስመጣት ብቻ አላበቁም። ግሪን ካርድ አስወጥተው ድርጎ መድበው ቤት አደላድለው ከመንግስት የሚገኘውን ጥቅማጥቅም አስከብረው የሁለት መንግስት ተጠቃሚ ለመሆንም አበቋቸው፡፡ ይገርማል፣ የዚችን ዐለም ከንቱነት መነኩሴውም ሳይቀር ሁሉም ዘንግቶታል ልበል? የነገው ቀን ለሳቸው ምን ይዞ እንደሚመጣ ሳያውቁ ወንድማቸው ላባቸውን ያፈሰሱበትን፣ አበሳ ያዩበትን ቤተክርስቲያን ለመቀማት ከዋሾ ፖለቲክኞች ጋር ተባብረው ወንድማቸውን ለማይዘልቅ ክብር ለሠላሳ ብር ሽጠው አረፉት፡፡ ነፍሳቸውን ይማራቸውና፣ በመኪና አደጋ ሕይወታቸ ያለፈው ጥሩ ክርስቲያን የሁሉ አባት የነበሩት የጥንቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳሰ ስም ከህልፈታቸው በኋላ በግብርም በዕምነትም ለማይመጥናቸው ሰው ተላለፈ፡፡
የክፉዎች ሥራ ሲያልቅ አያምር ነውና ከላይ ከፍ ብሎ የጠቀስኩላችሁ “የሲኖዱሱ ድጋፍ ሰጪ” ተብዬው ቡድን ከቦልቲሞር ከየአምባቸው ተሰብስበው በመጡ ካህናትና ሌሎች ፖልቲከኛ ነን ባይ ሕልመኞች ታጅቦ ለጊዜው የመጨረሻ እርምጃ አድርገው የወሰዱት በ ኦሃዮ ሠላሳ ሁለተኛውን የስደተኛው ሲኖዶስ ግማሽ ዓመታዊ ስብሰባ ረግጦ በመግባት ስብሰባውን መበጥበጥ ሆነ፡፡ የኦሃዮው የሲኖዶስ ስብሰባ ከጳጳሳት፣ ከመነኮሳትና ከካህናት በስተቀር ለሌላው ዝግ ሆኖ ሳለ እነዚህ እምነተቢስ ደፋሮች በማን ትብብር በሩንስ ለመርገጥ በቁ? መቼም ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው ይባል የለ፣ የሲኖዶሱ ዋና ጸሃፊ ከነዚሁ ኢትዮጵያዊነትንም ሆነ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ከማያውቁ ፖለቲከኞች ጋር ክመኖሪያቸው ከሳን ሆዜ ወደ ቦልቲሞር ከተማ የስድስት ሰዓት በረራ አድርገው የሴራው ስብሰባ ተካፋይ ሆነው እንድነበር ተሰማ፡፡ እንግዲህ በዚህ መንገድ ነበር ለሶስት ቀናት በተካሄደው የሃይማኖ አባቶች ስብሰባ ላይ አባቶቹ አፋቸው ተለጉሞ ምንም ቃል ትንፍሽ ሳይሉ የውሳኔ ሃሳብም ሆነ ቃለጉባኤ ሳይቀርብ እንደሚሸለት በግ በገዛ ስብሰባቸው ተመልካች ሆነው የተመለሱት፡፡ ስብሰባውን ተካፍለው የተመለሱት የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ስለስብሰባው ለምዕናን ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ስብሰባው በሠላምና በወንድማማችነት መንፈስ መፈጸሙን የሀሰት ብሥራት ሲያበሥሩ እራሳቸው ያለሟቸውን ነጥቦች በስብሰባው ላይ የተወሰኑ በማስመሰል አውደምሕረት ላይ ቆመው ጉድ እየተባለ ዐይናቸውን በጨው አጠበው ያለህፍረት አነበነቡ፡፡ ከወጥ ቤት ሃላፊነት ወደ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበርነት ዕድገት ያገኙት እኒሁ ሰው ላስሾማቸው ቡድን ታማኘነታቸውን በሚገባ ለማስረገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይመስላል፡፡
የአመራር ለውጥ ጥያቄ በሕዝብ ዘንድ መንሳፈፍ ከጀመረብት ግዜ አንስቶ ይህ የሲኖዶሱ ስብሰባ እስተካሄደብት እስካሁኑ ግዜ ድረስ ቢያንስ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ ክብሩ ይስፋና በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ ብዙ ለማየት አብቅቶናል፡፡ ማን የእግዚአብሔር ካህን ማን የተቃራኒው እንደሆነ፤ ማን ኃይማኖተኛ ማን ፖለቲክኛ፤ ማን አማኝ ማን ከሀዲ እንደሆነ ለማየት ታድለን ነበር፡፡ መንገዳቸውን በሃይማኖታቸው ያስተካከሉ ባዕታቸውን የዘጉ ግዜያቸውን፣ አገልግሎታቸውን ለአምላካቸው ብቻ የሰጡ ብጹአን መነኮሳት አባቶች የመኖራቸውን ያህል ባንፃሩ ደግሞ በስተርጅና ዕድሜያቸው የሃይማኖት አባትነታቸውን እንዳሮጌ ካባ በመጣል ጭልጥ ብለው ወደ ፖለቲካው መስመር መግባታቸው የጴጥሮስነት ሃላፊነታቸውን በመርገጥ ዋናፀሐፊው ሲኖዶሱን የግላቸው ሥልጣን ማእከል፣ የፖለቲከኞች ቁማር መጫወጫ ማድረጋቸው በምዕመን ዘንድ አልተወደደላቸውም፡፡ እግዚአብሔርስ ቢሆን ቤቱን ቄሳር ሲጓደድበት ይወዳል ብላችሁ ነው?
ወንድማችሁ ኃይለገብርኤል ታደገ
This self appointed papas or as he wants to be called “Abatachen” is a fraud and a politician in a robe. If he was a true Christian and one who has studied the Bible, he would not have approved the name “Abatachen”, which belongs to the one and the only father, The LORD. Matthew 23:9 9 And call no man your father on earth, for you have one Father, who is in heaven.
If you study the history of this man (Abunu Melke Sadiek), he has always been a puppet of the Ethiopian Monarchy. He has been a politician all his life. His commitment to his faith, church, and believers of the Orthodox religion has been non existent. Ever since he had fled Ethiopia, he has been campaigning against the Papas in Ethiopia for the sole purpose of becoming “the Papas” than teaching Christianity, forgiveness and kindness.
For his part, he has been visiting churches all around the United States building consensuses against the Sinodos in Ethiopia, as he continues to live the extravagant life supported by a few corrupt board members and business people in Oakland, CA. At the height of his hypocracy , he and his corrupt supporters purchased a $680,000 (Birr 11,560,000) home for his sole use. ( more coming soon in how he help purchased this home fraudulently on the backs of elderly Ethiopians in the Bay Area.)
This is a defining moment to tell the truth about this corrupt individual. To maintain his lifestyle, cover up for his co-conspirators and corrupt supporters, he is in the process of destroying a church built by many faithful elderly Ethiopians, protectors of the Orthodox faith, and those genuinely interested in learning The Word of God. Through his campaign of intimidation, character assassination, false accusation, mixing religion with politics for the shear purpose of garnering support for his unquenchable thirst for supremacy, he is attempting to tear down the career of a beloved teacher, educated and enlightened servant of God — Aba Kaletsedke. (more on this coming soon.)
What Christians must do to stop this renegade man on his tracks?
Stop supporting him and his co-conspirators. Do not help him or churches led by him. When the money stops coming, he won’t be able to continue his evil deeds. Members of the Oakland/Bay Area Church led by him and his co-conspirators, please start redirect your giving to something worthwhile. Find poor people in Ethiopia (in your old neighborhood) and send them some money. There are millions of homeless orphans in our country that will be happy to use a portion of the 11,000,000 Birr wasted on the vacant villa purchased for “abatachen”.